ከ430 በላይ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ

ከ430 በላይ ስደተኞች ሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ ከመስመጥ ያተረፈው የርዳታ ድርጅት መርከከቦች ዛሬ በጣሊያኗ ሲሲሊ ደሴት ላይ እንዲያርፉ ተፈቀደላቸውት። የጣሊያን መንግሥት ፍቃድ የሰጠው በተለይ ሜዲትራኒ ከተሰኘው የጣሊያን የርዳታ ድርጅት የመጨረሻ የትብብር ጥያቄ ከቀረበለት በኋላ ነው። ስደተኞችን ከባሕር መስጠም ካተረፉት አንዱ የጣሊያኑ መንግሥታዊ ያልሆነው ሜዲትራኒ የተሰኘው ድርጅት መርከብ ማሪ ጆንዮ ለጣሊያን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር በ10 ሰዓታት ውስጥ የሚያርፍበት ወደብ ካልተፈቀደለት በቅርቡ ወደሚገኘው ወደብ ሄዶ ለማረፍ እንደሚገደድ አስጠንቅቆ ነው የጻፈው። ይኽን ተከትሎም በደቡባዊ ሲሲሊ ፖዛሎ ወደብ ላይ እንዲያርፍ ተፈቅዶለታል። መርከቡ ከሊቢያ እና ማልታ ዓለም አቀፍ የውኃ አካባቢዎች ባለፈው እሑድ እና ሰኞ ዕለት ባካሄደው ቅኝት ከመስጠም ያተረፋቸውን 92 ስደተኞች መጫኑ ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥም 30 ብቻቸውን የመጡ ሕጻናት ይገኙበታል። በተመሳሳይ የጀርመኑ የረድኤት ድርጅትም ከባሕር ላይ ያተረፋቸውን 352 ተሰዳጆች እንደጫነ ለአራት ቀናት ማረፊያ አጥቶ ከቆየ በኋላ በዚሁ ፖዛሎ ወደብ እንዲያርፍ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ሲዎች 3 በተባለችው መርከብ ላይ ደግሞ ወላጆቻቸው አብረዋቸው የሌሉ 120 ልጆች ይገኛሉ ነው የተባለው። ሁለቱም የርዳታ ድርጅቶች የተንገላቱት ከአፍሪቃ የመጡት ስደተኞች ማረፊያ እንዳያገኙ ሆን ብሎ አስተጓጉሏል በሚል የጣሊያን መንግሥት ላይ ክስ አቅርበዋል። SOS ሜድትራኔ የተሰኘችው የጣሊያን የርዳታ ድርጅት መርከብ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 1000 ስደተኞችን በሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ከመስመጥ ማዳኗ ተገልጿል።

Design a site like this with WordPress.com
Get started